ክርስቶስን በመምረጣችንና የእርሱ ተከታዮች በመሆናችን የተለያዩ መከራዎች ሊደርሱብን ይችላሉ ክርስቶስ በዓለም እንደተገፋ እርሱን መስለው የሚኖሩትን ሁሉ ዓለም ትገፋለች ሆኖም አምላካችን ቀዳሚ ሆኖ ሄዶበታልና በሚያስፈልገን ጊዜና ቦታ ሁሉ በአጠገባችን ሆኖ ስለሚረዳን ልንበረታታና ልንፀና ይገባናል